የመድኃኒት ትርጉምና ዓይነቶች


አዘጋጅ፡ ኃይለማርያም ሸመልስ  

በጥቁር አንበሳ ስ/ሆስፒታል የመድኃኒት መረጃ  ባለሞያ


 

መድኃኒት  ማለት የሰውነት በሽታን ለመመርመር፣ ለማከም፣ ለማስታገስ፣ ወይም ለመከላከል የሚያገለግል ማንኛውም ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮቸ ውህድ ሲሆን እንደ መድኃኒት ሊያገለግሉ የሚችሉ የመድኃኒት ዓይነቶች  ናቸው።

 • የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች
 • ፕሪከሰር መድኃኒቶች
 • የባህል መድኃኒቶች
 • ተደጋጋፊ/አማራጭ መድኃኒቶች
 • መርዞች
 • ደምና የደም ተዋጽኦዎች
 • ክትባቶች
 • ጨረር አፍላቂ መድኃኒቶች
 • ኮስሞቲክሶችና የሳኒተሪ ዝግጅቶች እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎችን ያጠቃልላል።

መድኃኒቶች እንደ አወሳሰዳቸው፣  አሰራራቸው አሊያም ለታለሙበት የህክምና ዓላማ ዓይነት ሊለያዩ ይችላሉ። ይህንን ማወቅ ደግሞ በመድኃኒት ዙሪያ የሚከሰቱ ብዥታዎችን እና ሊከሰቱ የሚችሉ ተጓዳኝ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ አለው። በመሆኑም ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የመድኃኒት ዓይነቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።

1. በአወሳሰዳቸው (Route of Administration)

መድኃኒቶች በሚወሰዱበት መንገድ ዓይነታቸው ሊለያይ ይችላል።ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ዓይነት ቦታ እየተወሰዱ የአወሳሰዱ ሂደት ግን ሊለያይ ይችላል።ይህ ደግሞ ካለማወቅ የሚፈጠርን ስህተት ከመቀነስ አንጻር ጠቃሚነቱ የጎላ ነው።

 

በአፍ የሚወሰዱ ጠጣር የመድኃኒት ዓይነቶች
በአፍ የሚወሰዱ ጠጣር የመድኃኒት ዓይነቶች
በአፍ የሚወሰዱ ፈሳሽ የመድኃኒት ዓይነቶች
በአፍ የሚወሰዱ የነፋስ የመድኃኒት ዓይነቶች
ሀ. በአፍ የሚወሰዱ 

በአፍ የሚወሰዱ መድኃኒቶች  እንደአሰራራቸውና እንደታሰበላቸው የመድኃኒት አገልግሎት ሊለያዩ ይችላሉ ምንም እንኳ በአፍ ቢወሰዱም አወሳሰዳቸው ግን የተለያየ ነው። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-

 • በአፍ ተወስደው የሚዋጡና በአንጀት ውስጥ አልፈው ወደ ደም ውስጥ የሚገቡ፣
 • ለጨጓራ ህመም ታስበው በአፍ የሚዋጡ፣
 • በአፍ ውስጥ የሚቀመጡ ማለትም በምላሳችን የታችኛው ክፍል ወይም በጥርሳችንና በድዳችን መካከል የሚቀመጡ፣
 • በአፍ ተስበው ወደ ሳንባ የሚገቡ፣
ለ.በመርፌ የሚሰጡ

መድኃኒቶች በመርፌ ተደርገው ቀጥታ ወደ ደም ስሮቻችንና ሌሎች መላ አካላቶቻችን የሚሰጡበት መንገድ ሲሆን  እነዚህም በዓይነታቸው እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡-

በመርፌ የሚሰጡ የመድኃኒት ዓይነቶች
 • በደም ቧንቧ ውስጥ የሚወጉ፣
 • ከቆዳ ስር የሚወጉ፣
 • በጡንቻ ስር የሚወጉ፣
 • በጉልበት መገጣጠሚያ ውስጥ የሚወጉ፣
 • በህብለሰረሰር ውስጥ የሚወጉ፣
በአፍና በመርፌ ከሚወሰዱ በተጨማሪ ሌሎች ዓይነቶች  ያሉ ሲሆን እነዚህም
 • በቆዳ ላይ የሚለጠፉ
 • በፊንጢጣ የሚወሰዱ
 • በማህፀን ውስጥ የሚወሰዱ
 • በዓይን፣በጆሮ አሊያም በአፍንጫ ላይ ተደርገው የሚወሰዱ ወዘተ— ተጠቃሽ ናቸው።

2.በአሰራራቸው (Dosage form)

መድኃኒቶች  በአሠራራቸው ይለያያሉ ሲባል መድኃኒቶቹ የሚወሰዱበት የመጨረሻ ውጤት የዓይነት ልዩነት አላቸው ማለት ነው እነዚህንም ስንመለከት፡

ሀ. ጠጣር (Solid) መድኃኒቶች
ለ. ግማሽ ጠጣር (Semi Solid) መድኃኒቶች
ሐ. ፈሳሽ (Liquid) መድኃኒቶች
ሐ. የነፋስ (Gas) መድኃኒቶች

በዚህ ዓይነት መድኃኒቶች ተሰርተው ለተጠቃሚው በገበያው ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ ይህ ማለት አንድ መድኃኒት አንድ ዓይነት የአሠራር ዓይነት ብቻ ሳይሆን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የአሰራር ዓይነት  ሊኖረው ይችላል።

 1. በታለሙበት ዓላማ (purpose)

መድኃኒቶች ከጅምሩ ሲዘጋጁ የአንድን ሰው ሆነ እንስሳ አሊያም ሰብል ጤንነት ለመጠበቅና ለማስቀጠል ሲባል ሊወሰዱ ይችላሉ።በመሆኑም የታለሙበት ዓላማ ብዙ ዓይነት ከመሆኑ አንጻር መድኃኒቶችም እንደዚያው የተለያዩ የሚሆኑበት ወቅት ይሰፋል።ከስር በስፋት የሚታዩት እንደምሳሌነት እንመልከት።

 • የፀረ-ተዋህስያን
 • የፀረ-ወባ
 • የስኳር
 • የልብና ደም ስር
 • የአስም
 • የኤች አይ ቪ/ኤድስ
 • የካንሰር ወዘተ. . . .

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ አንድ መድኃኒት ከታለመበት ዓላማ፣ የአሰራር ዓይነት እና የአወሳሰድ መንገድ ሊለያይ ስለሚችል ይህንን ልዩነት በመረዳት በእውቀት ላይ የተመሰረተ የመድኃኒት አጠቃቀም ባህል ማድረግ ይገባል። ይህንን ለማዳበር ከሚረዱ ነጥቦች መካከል፡-

 • ሐኪሞችን የታዘዘው የመድኃኒት ጥቅም ምን እንደሆና አወሳሰዱንም መጠየቅ፣
 • የመድኃኒት ባለሙያው በሚያሳየው መንገድ መውሰድ፣
 • በመድኃኒቱ ውስጥ የሚገኘውን የእሽግ ጽሁፍ (leaflet) ስለመድኃኒቱ ተጨማሪ ዕውቀት ለማግኘት ማንበብ፣ማንበብ ካልቻሉም ማስነበብ፤
 • ከመድኃኒቱ ጋር የሚጋጭ ወይም የሚመከር የአኗኗር ስልት፣ የአመጋገብ እና የአወሳሰድ ሥርዓት አለመጠቀም፣ ሐኪሞችንና የመድኃኒት ባለሙያ መጠየቅ።
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s