በመድኃኒት አጠቃቀም ዙርያ የሚታዩ ስህተቶች


አዘጋጅ፡ ኃይለማርያም ሽመልስ 

የመድኃኒት መረጃ ማእከል ፋርማሲስት 

ውድ አንባብያን በአብዛኛው ታካሚዎች በመድኃኒት አጠቃቀም ዙርያ የሚታዩ ስህተቶች እና ስለመፍትሔዎቻቸው የሚያስረዳ አስተማሪ ጽሑፍ እነሆ፡፡ ጽሑፉን በማንበብ እና በማስነበብ የሕብረተሰባችንን በመድኃኒት ዙርያ ያለውን ንቃተ ሕሊና እንዲጎለብት ብሎም በመድኃኒት አጠቃቀም ዙርያ ለሚከሰቱት ችግሮች መረጃውን በማካፈል የበኩልዎትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናሳስባለን፡፡

 1. እርስ በርስ የሚጋጩ መድኃኒት (ምግብና መጠጥ) አብሮ መውሰድ
  • አንዳንድ መድኃኒቶች እርስ በርሳቸው አሊያም ታካሚዎች ከሚበሏቸው ምግብና መጠጦች የሚጋጩ በመኖራቸው ከመውሰዳቸው በፊት ዶክቶር ወይም ፋርማሲስትን በጋራ ስለሚወስዷቸው መድኃኒቶችን መጠየቅ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ቴትራሳክሊን የተሰኘው መድኃኒት ሲወሰድ ወተት ቢጠጣ ወተቱ የመድሃኒቱን የማሻል አቅም በማደናቀፍ ኃይሉን ይቀንሰዋል፡፡
   1. መፍትሔ፡- አንዳንድ መድኃኒቶች እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸው በፊት ዶክቶር ወይም ፋርማሲስትን በጋራ ስለሚወስዷቸው መድኃኒቶችን መጠየቅ ይገባል፡፡ ስለአመጋገብ ሁኔታዎች ለምሳሌ ስለሚከለከሉ ወይም ከመድኃኒቱ ጋር አብረው መወሰድ ያለበት የአመጋገብ ስልት ታካሚዎች ባለሞያውን መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡

      

 1. ከምርመራ ክፍል ያለ በቂ (አነስተኛ) በመድኃኒት ዙርያ መረጃ ይዞ መውጣት
  • በብዙ ታካሚዎች ከሚታዩ ችግሮች መካካል አንዱ የሆነው የሕክምና አገልግሎት ከተረከቡበት የምርመራ ክፍል ሲወጡ ስለታዘዘላቸው መድኃኒት ምንም ዓይነት መረጃ አለመጠየቃቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ሊጠይቁ ከሚገባቸው መረጃዎች ቢያንስ የታዘዘው መድኃኒት ስም፣ የታዘዘበት ዓላማ የአወሳሰድ ሒደቱ ወዘተ. . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡
   • መፍትሔ፡- ከሐኪም ምርመራ ከፍል ከመውጣትዎ በፊት ስለሚወስዱት መድኃኒት ስም፣ ለምን እንደታዘዘ እና እንዴት፣ በምን ያህል መጠን መወሰድ እንዳለበት ጠይቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የጽሑፍ ማብራሪያ መያዝ የመረጃ ክፍተትን ይሞላል፡፡ 

 1. መድኃኒቱ በታዘዘበት መንገድ አለመውሰድ
  • በሐኪም ታዝዞ በመድኃኒት ባለሞያ የተሰጠውን መድኃኒት በአግባቡ በታዘዘው መልኩ መድኃኒት አለመውሰድ ሌላኛው በታካሚዎች ላይ የሚታየው ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የእንክብል መድኃኒቶች በፈንጣጣ አሊያም በማሕፀን የሚወሰዱ መድኃኒቶችን በአፍ መዋጥ፣ ተበጥብጦ የሚጠጡ ፈሳሽ መድኃኒቶችን ሳይበጠብጡ መውሰድ፣ ወዘተ. . .
   • መፍትሔ፡- ከጤና ባለሞያ ስለመድኃኒቱ አወሳሰድ የሚሰጠውን ምክር በጥሞና ማድመጥና ግር ያለ ነገር ሲኖር ማብራሪያ መጠየቅ፡፡ በተጨማሪም ከፋርማሲ ሲወጡ በጽሑፍ የተደገፈ ማብራሪያ ስለአወሳሰዱ መቀበል ማረጋገጥ፡፡
 1. መድኃኒቱ በታዘዘበት ወቅትና መጠን አለመውሰድ
  • መድኃኒት የታሰበለትን ዓላማ እንዲያሳካ ከሚያስፈልጉ ሁኔታዎች መካከል በአካላችን ውስጥ መድኃኒቱ በሚያስፈልግበት መጠን መገኘቱ ነው፡፡ ነገር ግን በታዘዘበት ወቅት እና መጠን መድኃኒት ባልተወሰደ ጊዜ በአካላችን ውስጥ የሚገኘው መጠን ሕመምን ለማከም ከሚጠበቀው በላይ ከፍ አሊያም ዝቅ ይላል፡፡
   • መፍትሔ፡- መድኃኒቱ በታዘዘበት ጊዜ ለመውሰድ እንዲረዳ ከመድኃኒት ባለሞያ መድኃኒቱን ለመውሰድ አመቺ ጊዜ መመካከር፡፡ ከዚህም ሌላ የመድኃኒቱ መወሰድ ካለበት መጠን በፍጹም ጨምሮ አሊያም ቀንሶ አለመውሰድ ይገባል፡፡
 1. መድኃኒቶችን በተገቢው ቦታ አለማስቀመጥ
  • መድኃኒቶች ጥራታቸው ጠብቀው እንዲቆዩ ተገቢ የአቀማመጥ ቦታ አላቸው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ መድሃኒቶች በማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ ሲኖርባቸው ሌሎች ደግሞ በከባቢ አየር ሙቀት ባላቸው ስፍራ በመቀመጥ አለባቸው፤ ሌሎች ከቀጥታ የፀሐይ ጨረር መጠበቅ ሲኖርባቸው ሌሎች ደግሞ ከእርጥበት መጠበቅ ለመድኃኒቱ ጥራትና ብቃት አለባቸውሕጻናት በማይደርሱበት ቦታ አለማስቀመጥ፡፡ ነገር ግን ታካሚዎች መድኃኒቶችን የት ማስቀመጥ እንዳለባቸው ባለመረዳታቸው ተገቢ ባልሆነ ቦታ ያስቀምጣሉ፡፡

 • መፍትሔ፡- የመድኃኒት ባለሞያውን እንዴት እና የት መድኃኒቱን ማስቀመጥ እንደሚገባ በመጠየቅ የሚሰጠውን ምክር በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ፡፡ የትኛውን መድኃኒት ሕጻናት በማይደርሱበት ቦታ ማስቀመጥ፡፡
 1. በመጨረሻም የትኛውንም ዓይነት መድኃኒቶችን አብሮ ከአልኮል ጋር መውሰድ አይገባም

 

Advertisements

2 thoughts on “በመድኃኒት አጠቃቀም ዙርያ የሚታዩ ስህተቶች

 1. በብዙ ታካሚዎች ከሚታዩ ችግሮች መካካል አንዱ የሆነው የሕክምና አገልግሎት ከተረከቡበት የምርመራ ክፍል ሲወጡ ስለታዘዘላቸው መድኃኒት ምንም ዓይነት መረጃ አለመጠየቃቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ሊጠይቁ ከሚገባቸው መረጃዎች ቢያንስ የታዘዘው መድኃኒት ስም፣ የታዘዘበት ዓላማ የአወሳሰድ ሒደቱ ወዘተ. . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡

  መፍትሔ፡- ከሐኪም ምርመራ ከፍል ከመውጣትዎ በፊት ስለሚወስዱት መድኃኒት ስም፣ ለምን እንደታዘዘ እና እንዴት፣ በምን ያህል መጠን መወሰድ እንዳለበት ጠይቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የጽሑፍ ማብራሪያ መያዝ የመረጃ ክፍተትን ይሞላል፡፡

  if the physician counsels the patient on medication related issues, what is the role of the pharmacist? Keeping the store and throwing prescribed drugs through the small window?
  It is known that government schools of pharmacies provide 5 year long education although the private ones are graduating students by 3 years. What was that long year education required?
  explanation for this is required?

  1. Dear @Dagmawi If you read via the entire article you will find solutions regarding the problem of patients not asking about their condition i.e. communication problem. In each section the article empowers the patient to effectively use the services of the health care providers.

   For Example Section 3 states how to use the role of pharmacists in order to alleviate the stated problem ከጤና ባለሞያ ስለመድኃኒቱ አወሳሰድ የሚሰጠውን ምክር በጥሞና ማድመጥና ግር ያለ ነገር ሲኖር ማብራሪያ መጠየቅ፡፡ በተጨማሪም ከፋርማሲ ሲወጡ በጽሑፍ የተደገፈ ማብራሪያ ስለአወሳሰዱ መቀበል ማረጋገጥ፡፡

   However, your question states “if the physician counsels the patient on medication related issues, what is the role of the pharmacist?”
   This implies the physician does not have the obligation on counseling about the patients problems and their medication.

   But this type of thinking is misleading one because most of the pharmacies have A high patient load so for the pharmacist to tell about every aspect of the clients ailment and the treatment is not applicable in the current Ethiopian situation.

   Furthermore the current prescription handed by most of the health facilities does not even include basic patient information such as diagnosis. so How is it only the duty of the pharmacist to counsel the patient on medication related aspect with out the proper patient background information which the physician knows in depth?

   So to solve the dilemma of the Ethiopian medication use problem the physician, the pharmacist and other allied health professional should be working together as a team not as a separate entity for the patient.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s